Friday, February 4, 2011

የፈረንጅ አበሻም አለ ለካ !

ሁሉም ሳይሆኑ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን አበሾች ወደ ውጪው አለም ሲወጡ ባህርያቸውን አለባበሳቸውን፤ ባሕላቸውን ሃማኖታቸውን ይለውጣሉ፡፡ ስልጣኔው የራስ የሆነውን ነገር ሁሉ መተው ሰለሚመስላቸው ከተፈጥሮ ቀለማቸው በስተቀር ሁለመናቸውን ይለውጣሉ፡፡ ኢትዮጲያዊ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ ከውስጣቸው በማጥፋት አስኪገርም ድረስ ማንንታቸውን ያጣሉ ፡፡ደሞ ከአበሻ ጋር ፤ የአበሻን ፊቱን አያሳየኝ ወዘተ ... የሚሉትን አባባሎች የምሬት ቃላቶቻቸው ያደርጋሉ፡፡ የተወለዱባትንም አገር ኢትዮጵንም እንደ ሌላ ባእድ አገር ማየት ይጀምራሉ፡፡
ሌላው የአበሻ ዘር ደግሞ ባይወለድባትም የእናት አባቴ ፤ ያያት የቅድማያቴ አገር እያለ ስለ ኢትየጵያና ወገኖቹ ብዙ መልካም ነገር ሲናገር፤ ሲጽፍና ሲያወድስ ይሰማል፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና እናት የተባለች ኢትዮጵያ ሁሉንም አይነት ሰው አፍርታለች ይዛለች፡፡ 
ነጭ ቀለም ያላቸው አንዳንድ ፈረንጆች በአባቶቻቸውንና በእናቶቻቸው ምክንያት ኢትዮጵያ ሲወለዱ ደግሞ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ግምትና ስሜት ምን እንደሚመስል ከሜዲያ ያገኘነውን ቁም ነገር ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል ብለን ስለገመትን አቅርበነዋልና ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን፡

http://www.dw-world.de/popups/popup_single_mediaplayer/0,,14815728_type_audio_struct_12103_contentId_6427031,00.html

Monday, January 31, 2011

ለመልአከ ሣህል አወቀ አሸኛኘት ተደረገላቸው !
በኤፕሪል 25 2010 የዳላስ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል አስተዳደር ቦርድ መልአከ ሣህል አወቀን በውድቅት ሌሊት በፖሊስ አስገድዶ በማስፍረም በክህነት ከሚያገለግሉበት የሥራ ገበታቸው ላይ እዲሰናበቱ ማድረጉ ይታወሳል፡፡ ይህንኑ የግፍ አሠራር በመመልከት ቀሲስ መስፍንም ሕዝቡን በዓውደ ምህረት ተሰናብተው በገዛ ፈቃዳቸው ሥራቸውን በመልቀቅ መውጣታቸውም ይታቃል፡፡ ይህንኑ ተከትሎ በተፈጠረ ውዝግብ የአስተዳደር ቦርዱ የቀጠራቸው ኬጂ 9 ቦምብ ፈታሽ ፖሊሶች ወደ ቤተ መቅደሱ በድፍረት ከነጫማቸው በመግባት ምእመናን ከጸሎት ገበታ ላይ በኃይል በመጎተት ደብድበዋል፤ በካቴና ብረትም ጠፍረው በማሰርም አሰቃይተዋል፡፡ ይህም በቴሌቪዥን የታየ ፤ ዓለምን ያስደነቀና ያስቆጣ አስገራሚ ክስተት ብዙዎችን ከቤተክርስቲያኒቱ አሽሽቷል፤አንዳንዶቹንም ሃይሞኖታቸውን እንዲቀይሩ አድርጓል፤ በርካታ የቤተክርስቲኒቱ ምእመናንም በመተባበር ድርጊቱንና አምባገነናዊውን የቦርድ አስተዳደርን በሕግ በመቃወም ጉዳዩን ፍርድ ቤት እንዲመለከተው አድርገዋል፡፡ 

Friday, December 3, 2010

አሜሪካኖች ባል ለሚስቱ ምን ያድርግ ይላሉ?
ከሰላዩ ብእር የቀጠለ
ክፍል አራት
ለባለቤቴ እጅግ ጥሩ ባል መሆን እንዳለብኝ ገና ድሮ በወጣትነት ዘመኔ ሳላገባ በፊት አስብ ነበር ፡፡ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሀሳብ ብዙ መጻሕፍትን እንብቤአለሁ፡፡ ካነበብኩዋቸው መጻሕፍት ብዙ ዕውቀትና ምክርንም አግንቻለሁ፡፡ ለዚህ ነው ባለቤቴን በተቻለኝ ሁሉ ለማስደሰትና ለመንከባከብ ጥረት ያደረኩት ፡፡ ከባለቤቴ ጋር የነበረንን የሆቴል ቤት ቆይታ ትርኢት ከማጠቃለሌ በፊት ምናልባት አንባቢያን ትምህርት ታገኙበት ይሆናል በማለት አንድ መጽሔት ሳነብ ካገኘሁት ላካፍላችሁ ብዬ ይህንን የእንጊሊዘኛ ጽሑፍ ጋብዤአለሁና አንብቡት ፡፡የተዘረዘረውን ሁሉ ለመፈጸም ቢከብድም ጽሑፉ በትዳር ሕይወት ውስጥ ከሚስት ጋር ሰላማዊ ኑሮን ለመምራት ባል ማድረግ ያለበትንና ሚስት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ የሚዘረዝር ነውና አንብባችሁ የራሳችሁን ግንዛቤ ውሰዱ ፡፡