እዚህ ይጫኑበአስተዳደር ቦርድ ችሎታ ማነስ ምክንያት እየደረሰ ያለውን ከፍተኛ ጥፋት በወቅቱ ለማስቆምና የሚበጀውን ሰላም ለማምጣት ሲሉ ግለሰቦች ፤ሽማግሌዎችና የሰላም ልዑካን ሁሉ ብዙ ጥረት ቢያደርጉም ድካሙ በአስተዳደር ቦርዱ እምተኝነት ምክንያት ሳይሳካ ቀርቷል፡፡ ይሁን እንጂ ጥረቱን በመቀጠልና ተስፋ ባለመቁረጥ የቤተክርስቲያኑ የወደፊት ሁኔታና ዕጣ እጅግ አድርጎ ያሳሰባቸው ቁጥራቸው ከ35 በላይ የሚሆኑ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት ለተፈጠረው ችግር መፍትሔ ለመሻትና ሌሎች ጉዳዩ ይመለከተናል የሚሉትን አባላት ሁሉ ጨምረው ለመወያየትና በጋራ መፍትሔ ለመፈለግ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ጥያቄ በጽሑፍ ቢያቀርቡም የአስተዳደር ቦርዱ በተለመደው የእንቢተኝነት ባሕርዪው አዳራሹን መጠቀም እንደማይችሉ በመግለጽ ከልክሏል፡፡
ሰላም ተዋሕዶ - ትምህርታዊ የሆኑ የተለያዩ መንፈሳዊ ጽሑፎችን ፤ ዘገባዎችን ፤ በሕብረተሰባችንና በሌላው ዓለም ሕዝብ ባህልና ሕይወት ውስጥ የሚመላለሱ ወጋወጎችን የምታስነብ አስተማሪ ፤ አዝናኝና ቁም ነገር አዘል ብሎግ ናት፡፡Blogging Since Oct 2009
Tuesday, June 8, 2010
Monday, June 7, 2010
ሠበር ዜና !
የዳላሰ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ ጸሐፊና የውብ እንጀራ ባለቤት የሆኑት አቶ አበበ ጤፉ ከሌሎች ባልደረቦቻቸው ጋር በመሆን በቤተክርስቲያኒቱ ላይ ያደረሱት የከፋ የአስተዳደር በደል 90% በሚሆኑ አማንያን ዘንድ እጅግ እንዲጠሉ አድርጓቸዋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለአካካቢው ነዋሪ በየመደብሩ የሚያስቀምጡት የውብ እንጀራ ገዢ አጥቶ በመበላሸት እየተጣለ እንደሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡ ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ እንዲሉ አቶ አበበና አጋሮቻቸው የቤተክርስቲያኒቱን ካህን ያለአግባብ ከሥራ ያሰናበቱትና ፖሊስ በመቅጥር ሕዝቡን ያስደበደቡት ገና ወደ ቦርድ በገቡ በሦስት ወራቸው እንደሆነ ይታወቃል፡፡
Tuesday, June 1, 2010
ማኅበረ ቅዱሳን ጉባዔውን በመልካም ሁኔታ ጀምሮ አጠናቀቀ !
በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው የማኅበረ ቅዱሳን 12ኛ መደበኛ ጉባዔ በዳላስ ከተማ ተካሄደ ፡፡
ከ May 28 - 30 ድረስ በቆየው በዚሁ ጉባዔ የዓመቱ የማኅበሩ ሥራዎች ግምገማ ሪፖረት የቀረበ ሲሆን የቀጣዩን ዓመት የሥራ ዕቅድና በጀትንም አጽድቋል፡፡http://www.timeanddate.com/worldclock/fullscreen.html?n=7
;አስካሁን ከተደረጉት የማኅበሩ ዓመታዊ ጉድባዔያት በዐይነቱና በይዘቱ ከፍተኛ ነው በተባለው በዚሁ ጉባዔ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ኤዎስታጤዎስ የተገኙ ሲሆን ከተለያዩ የአሜሪካን ግዛቶች በርከት ያሉ ካህናትና ከመቶ ሃያ በላይ የሚሆኑ የማኅበሩ አባላት በተወካይነት ተካፋይ ሆነዋል ተብሏል፡፡
ይህንኑ የሰሜን አሜሪካ 12ኛውን ዓመታዊ በዓል ምክንያት በማድረግ May 31 2010 በክራውን ፕላዛ ሆቴል ውስጥ በተዘጋጀው ትምህርታዊ ጉባዔ ቁጥሩ ከ 200 በላይ የሚሆን ህዝብ የተገኛ ሲሆን ስለ ማኅበረ ቅዱሳን አመሠራረትና ማኅበሩ በቤተክርስቲያን ውስጥ ስላለው ተሳትፎ ከማኅበሩ ምሥረታ ጀምሮ በነበሩና ማኅበሩን በከፍተኛ ሁኔታ እያገለገሉ ባሉ አባቶችና ወንድሞች ሰፊ ገለጻና ትምህርት ተሰጥቷል፡፡ በዚሁ ትምህርታዊ ጉባዔ መልአከ ሳሌም አባ ገብረ ኪዳን ፤ መልአከ ሰላም ቀሲስ ያሬድ ገብረ መድኅንና ዲያቆን ኤፍሬም እሸቴ በተጋባዥ መምህርነት ተሳትፈዋል፡፡
በዚሁ ጉባኤ ማህበረ ቅዱሳን በኢትዮጵያም ሆነ በውጭው አለም ለቤተክርስቲያኒቱ ያበረከተውንና እያበረከተ ያለው የሙያ፤የገንዘብ፤የጉልበትና የስብከተ ወንጌል አገልግሎት በእውነተኛዪቱ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ሁሉ እንዲወደድና እንዲደገፍ ያደረገው ቢሆንም የቤተክርስቲያናችን መሠረታዊ ጠላቶች የሆኑ መናፍቃንና አስመሳይ ፖለቲከኞች ግን የስም ማጥፋት ሥራዎችን እንደተያያዙትም ተገልጧል፡፡ ይሁን እንጂ ሕዝቡም ለመናፍቃንና ለእነዚህ አስመሳይ ፖለቲከኞች ፕሮፓጋንዳና የሐሰት ወሬ ጆሮውን እንደማይሠጥና ዳግመኛ እንደማይወናበድ ውስጣዊ ስሜቱን በቁጭትና በቃላት ገልጧል፡፡
በመጨረሻም ሕዝቡ ስለቤተክርስቲያን አጠቃላይ ገጽታዎች ግንዛቤንና እውቀትን እንዲያገኝ እንዲህ ዓይነት ጉባዔያት በተወሰኑ ወራት ሊዘጋጁ እንደሚገባ በማሳሰብ የጉባዔው ፍጻሜ ሆኗል፡፡
Subscribe to:
Posts (Atom)