Wednesday, May 11, 2011

አሰቸኳይ መልእክት ለኢ-ሜይል 
ተጠቃሚዎች በሙሉ !
በአልቃይዳው መሪ በኦሳማ ቢላዲን መገደል ምክንያት ለበቀል የተዘጋጁ አሸባሪዎች ከትናት ማክሰኞ እለት ጀምረው የመርዝ ቫይረሶቻቸውን በዓለም ንጹሐን ዜጎች ኮምፒውተሮች ላይ በኢሜል በመልቀቅ የተለመደ የጥፋት ተግባራቸውን አሁንም ቀጥለውበታል ፡፡በዚህ መሠረት ኦሳማ ቢላዲን በስቅላት እንዶሞተ ተዶርጎ በተሠራ የሐሰት ፎቶግራፍ ና ይህንኑ በሚገልጽ ('Osama Bin Laden Captured' or 'Osama Hanged',) በሚል ርእስ የተዘጋጀ ኮምፒውተርን የሚሰብር አዲስ ቫይረስ በአለም መለቀቁን McAFree የተባለው የማይክሮሶፍት ካምፓኒ የኮምፒውተር ቫይረስ መከላከያ ክፍል አስታውቋል፡፡
ቫይረሱ ኢሜል አታችመንት ፋይል ውስጥ ተቀምሞ የተሠራጨ ሲሆን ጠቃሚ የሆኑ መረጃዎች የሚቀመጡበትን የኮምፒውተሩን ሃርድ ዲስክ እንዳይጠገን አድርጎ የሚሠብርና የሚያበላሽ ነው ፡፡ ስለዚህ በኢሜል ፋይላችሁ ውስጥ በሚገኝና በምታውቁትም ሆነ በማታውቁት ሰው አድራሻ የሚመጣ እንዲህ ዓይነቱን ፋይል ዴሊት አድርጋችሁ ከማስወገድ ውጪ በምንም ዓይነት እንዳትከፍቱት በጥብቅ እያስገነዘብን መልእክቱን ላላገኙ የኢሜል ተጠቃሚዎች በቻላችሁት ሁሉ እንድታደርሱ ሰላም ተዋሕዶ ደንበኞቹዋን ታሳስባለች፡፡

No comments:

Post a Comment

አስተያየት