ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው ሲል ነቢዩ ዳዊት ተናግሯል፡፡ መዝ ፡፡የሰው ልጆችም ይህንን አምላካዊ ቃል ትርጉሙን በትክክል የሚረዱት ባልና ሚስት ሆነው በሚኖሩበት ቤታቸው ውሰጥ ከአብራካቸው የወጣ ህጻን ልጅ ሲያገኙ ነው፡፡ በምጥና በጋር ልጇን ለመወለድ የቀረበች ነፈሰ ጡር ሴት ልጇን በወለደች ጊዜ ምጥና ጋሯን በመርሳት በደስታ ትዋጣለች፡፡ አባትም እንደዚሁ፡፡
የተወለዱ ልጆች ከእንጭጭነት አልፈው ሲፋፉና ድክ ድክ እያሉ ሲወድቁ ሲነሱ ማየት ትልቅ የኅሊና ደስታን ይሰጣል፡፡ ይሁን እንጂ ልጆች በሁለትና በሶስት ዐመት እድሜ ላይ ሲደርሱ በአእምሮ፤ በአካልና በቋንቋ እድገት ቢያሳዩም ለጫወታ እያሉ የሚሠሯቸው አንዳንድ ሥራዎቻቸው የሚያስገረሙና የሚያስቁ ናቸው፡፡ በዚህ እድሜ ደግሞ የወላጆች ጥብቅ ክትትልም እጅጉን ያስፈልጋል፡፡ ልጆች በተለይ ዘወትር ከሚጫወቱበት የቤት ውስጥ ሥፍራ ሰወር ሲሉና ድምጻቸው ሲጠፋ በመጠራጠር የት እንዳሉና ምን እየሠሩ እንደሆነ በቅርብ መከታተል ተገቢ ነው፡፡ ዛሬ ለዚህ ጽሑፍ ምክንያት የሆነን < Family Fun > በመባል በእንግሊዘኛ እየታተመ በሚወጣው የቤተሰብ መጽሔት ላይ ያገኘው የአንድ ቤተ ሰብ ገጠመኝ ነው፡፡ ድርጊቱ እንዲህ ነው፡፡