እጅግ አስቸኳይ የስብሰባ ጥሪ
በዳላስ የሚገኘውን የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ከድሮው ጀምሮ በልማት እድገቱ እዚህ እስኪደርስ ድረስ በጉልበታችሁ የደከማችሁና በገንዘባችሁ የተራዳችሁ፤
አሁን ግን በአምባ ገነኑ ቦርድ አባላት አይደላችሁም ተብላችሁ የተሠረዛችሁ የቤተ ክርስቲያኑ መሥራች አባላት በሙሉ
የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየከፋና የክርስትናውን መንገድ እየለቀቀ በመምጣቱ ምክንያት እንዲሁም የተረገጠውን የአባላት ክርስቲያናዊ መብት በሕግ ለማስከበር ፍርድ ቤት በመቆም ፍትህን እየጠበቃችሁ ያላችሁ ወገኖች በሙሉ
ክህነታችሁ እውነተኛውን አምላክ ክርስቶስንና ሕዝቡን የሚያገለግል እንጂ በውሸት፤በክህደትና በዛገ ፖለቲካዊ አስተሳሰብ የተበላሸ የቦርድን አሠራር የሚደግፍ ሆኖ ባለመገኘቱ ምክንያት በግፍና በሐዘን ከአገልግሎት የታገዳችሁና የተለያችሁ ክቡራን አባቶቻችን ካህናት በሙሉ
የተወሰኑ የቦርድ አባላት እራሳቸውን በቡድን በማደራጀት የቤተክርስቲያኒቱን ገንዘብና ንብረትያላግባብ በማባከንና እንዲሁም በጥላቻና በበቀል ላይ ተመርኩዘው የሚሠሩትን ኢክርስቲያናዊ ሥራ በመቃወም እራሳችሁን ከቦርድ አባልነት ያገለላችሁና የቀድሞ የአስተዳደር ቦርድ አባላት የነበራችሁ በሙሉ፤
አረመኔው ቦርድ በሚፈጽመውና በመፈጸም ላይ በሚገኘው ግፍ ምክንያት ማታና ጧት በማዘን የምታለቅሱ የአጥቢያው ቤተክርስቲያን አማኞች አባቶችና እናቶች፤ወንድሞችና እህቶች በሙሉ
በአምባገነኑ አስተዳደና የአስተዳደሩን ክፉ ተግባር በተቃወሙ የቤተክርስቲያኒቱ አባላት መካከል የተከሠተውን ግጭትና የክስ ሂደት በሰላም ፤ በእርቅና በይቅርታ እንዲፈታ ሌት ተቀን የደከማችሁ የሠላም ልዑካንና የደብራችን ሽማግሌዎች በሙሉ፤
የደብሩን ሰላምና ፍቅር ወደ ቀድሞ ሥፍራው ለመመለስና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ዱብዳ ሆነው የወደቁትን ካባድ ችግሮች በጋራ ለማስወገድ እንዲቻል የፊታችን ቅዳሜ May 8 2010 ቀን 4.00 PM ላይ ታላቅ ሕዝባዊ ስብሰባ ተዘጋጅቷል ፡፡ ስለዚህ ሁላችንም ቀደም ሲል የነበሩ ልዩነቶቻችን ወደ ጎን በመተው ቤተ ክርስቲያኒቱን ከጉልበተኞችና ከአንባገነኖች ለማዳን በሚደረገው በዚህ ስብሰባ ላይ በመገኘት ክርስቲያናዊ ግዴታችንን በጋራ እንድንወጣ በእግዚአብሔር ስም እናሳስባለን፡፡
የሠላም አምላክ ስብሰባችንን ይባርክ !
የስብሰባው ጊዚያዊ አስተባባሪ ኮሚቴ
የስብሰባው ቦታ
Double Tree Hotel Dallas / Richardson
1981 North Central Expressway , Richardson
TX ,75080
972 808 5386