ውጥረት በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን !
በአባ ወልደ ትንሣኤ ለሦስት ወራት ወደ ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን መምጣት ምክንያት በርካታ ምዕመናን ያደረባቸው ስጋት ቀደም ሲል በሰላም ተዋሕዶ ብሎግ እንደ ተገለጸው ለስደተኛው ሲኖዶስ መንገድ ለመጥረግና ቤተ ክርስቲያኗን ለማስረከብ ተልእኮ እንደሚመጡ መዕምናኑ በትክክል በመረዳታቸው ነው። ቦርዱ በአውደ ምሕረቱ ላይ እየወጣ ይህንን ያለሕዝቡ ፈቃድ አላደርገውም እያለ እየዋሽ ውስጥ ውስጡን ግን ከዲያቆን አንዶዓለም ጋር በመሆን በስውር ጉዞ መጀመሩ፤ ሕዝቡን እንደ አሻንጉሊ እያታለለና እየተጫወተበት እንደሆነ የሚያሳይ ነው።
በዚሀ ምክንያት ይህን የዲያቆኑንና የአስተዳደር ቦርዱን የተንኮል ሥራ የተረዱ አንዳንድ መዕመናን ከእግዚአብሔር ይልቅ የሚያመልኩት ቦርድን ነው ወደሚባሉት አንድኛው ካህን ቤት በመሔድ ስለ አባ ወልደ ትንሣኤ መምጣት ጉዳይ ያላቸው አቁዋም ምን እንድሆነ እንዲያስረዱአቸው መጠየቃቸው ታውቆአል። ካህኑም ከዚህ ቀደም አባ ወልደ ትንሣኤን ዳላስ ቅዱስ ሚካኤል የሚመጡ ከሆነ እኔ የቤተ ክርስቲያኑን ቁልፍ አስረክቤ እሔዳለሁ እያሉ ሲፎክሩ የነበሩ ሲሆን ካህኑ ልጃቸውም በዚሁ ተመሳሳይ አቅዋም እንደነበረ የሚታወቅ ነው ። ይሁን እንጂ እነዚህ አቁዋም የለሽ አባትና ልጅ ካህናት የአስተዳደር ቦርዱ ባደረሰባቸው የማስፈራሪያ ቃል መሠረት በፍርሃት በ 90 ዲግሪ ተገልብጠው ስለ አባ ወልደ ትንሣኤ ትልቅነት ማስታውቂያ ተናጋሪ መሆናቸው ብዙኃኑን አሳዝኖአል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአባ ወደ ዳላስ መምጣት ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እያየለ በመምጣቱ እርሳቸውም እዚህ ቢመጡ ከፍተኛ ተቃውሞ እንድሚጠብቃቸው ለራሳቸው ተድውሎ ሊነግራቸው እንደታቀደ ምንጮች ይጠቁማሉ። በኢመርጀንሲ 911 ደውለው ፓትሮል ፖሊሶችን መጥራት እንጂ ከእንግዲሀ ወዲህ የጋርላንድ ሲቲ ፖሊስ ቢሮ የአስተዳደር ቦርዱን የፖሊስ እርዳታ ጥያቄ እንድማያስትናግድ በጠነከረ ሁኔታ መልስ መስጠቱ ታውቆአል።