Tuesday, February 15, 2011


ሰላማዊን ሰው ያለበደልና ጥፋቱ መግደል ቃየላዊ ኃጢኣት ነው !

በእስልምና ስም ክርስቲያኖችን ለማጥፋት የተነሱ አክራሪ ስላሞች ክርስቲያኖችን ለማጥፋት ሌት ተቀን እየደከሙ ነው፡፡ በሰላማውያን ሕዝቦች መካከል ቦምብ በማፈንዳት በሕዝብ ሕይወትና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው፡፡የጥፋት ስልቶቻቸውን በየጊዘዌ በመቀያየር ሲከፈት ብናኙ ሰው የሚገድልና አንትራክስ የሚባል ገዳይ መርዝ በፖስታ በማሽግ ብዙ ሕዝብ በተለይም በረካታ አሜሪካውያን ሕይወታቸው ያለአግባብ እንዲያልፍ አድርገዋል፡፡

 አሁን ደግሞ Tide በሚልየልብስ ማጠቢያ ሳሙና ውስጥ ሲከፈት ሽታው የሰው ሕይወት ወዲያው የሚያጠፋን አንትራክስ መርዝ በመጨመር ከፖስታ ቤት የመጣ የአደራ እቃ በማስመሰል በየሰው ቤት በራፍ ላይ በማስቀመጥ ሰውን ለመግደል እየሞከሩ ነው፡፡ በቅርቡ የወጣው የ CNN ዜና እንደዘገበው ቁጥራቸው ወደ 7 የሚደርሱ አሜሪካውያን በዚሁ አደጋ መሞታቸውን ዘግቧል፡፡
ስለዚህ በየቤታችሁ በራፍ ላይ ከፖስታ ቤት የመጣ የሚመስል ነገር ስታዩ በጥንቃቄ በመመርመር ጉዳዩን እንድታጤኑና ሕይወታችሁን ከድንገተኛ ሞት እንድትጠብቁ ሰላም ተዋሕዶ በጥብቅ ያስገነዝባል፡፡

Friday, February 4, 2011

የፈረንጅ አበሻም አለ ለካ !

ሁሉም ሳይሆኑ ጥቂት የማይባሉ ኢትዮጵያውያን አበሾች ወደ ውጪው አለም ሲወጡ ባህርያቸውን አለባበሳቸውን፤ ባሕላቸውን ሃማኖታቸውን ይለውጣሉ፡፡ ስልጣኔው የራስ የሆነውን ነገር ሁሉ መተው ሰለሚመስላቸው ከተፈጥሮ ቀለማቸው በስተቀር ሁለመናቸውን ይለውጣሉ፡፡ ኢትዮጲያዊ የሚያሰኘውን ነገር ሁሉ ከውስጣቸው በማጥፋት አስኪገርም ድረስ ማንንታቸውን ያጣሉ ፡፡ደሞ ከአበሻ ጋር ፤ የአበሻን ፊቱን አያሳየኝ ወዘተ ... የሚሉትን አባባሎች የምሬት ቃላቶቻቸው ያደርጋሉ፡፡ የተወለዱባትንም አገር ኢትዮጵንም እንደ ሌላ ባእድ አገር ማየት ይጀምራሉ፡፡
ሌላው የአበሻ ዘር ደግሞ ባይወለድባትም የእናት አባቴ ፤ ያያት የቅድማያቴ አገር እያለ ስለ ኢትየጵያና ወገኖቹ ብዙ መልካም ነገር ሲናገር፤ ሲጽፍና ሲያወድስ ይሰማል፡፡ የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነውና እናት የተባለች ኢትዮጵያ ሁሉንም አይነት ሰው አፍርታለች ይዛለች፡፡ 
ነጭ ቀለም ያላቸው አንዳንድ ፈረንጆች በአባቶቻቸውንና በእናቶቻቸው ምክንያት ኢትዮጵያ ሲወለዱ ደግሞ ለኢትዮጵያ ያላቸውን ግምትና ስሜት ምን እንደሚመስል ከሜዲያ ያገኘነውን ቁም ነገር ጠቃሚ ትምህርት ይሰጣል ብለን ስለገመትን አቅርበነዋልና ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን እንዲያደምጡ እንጋብዛለን፡

http://www.dw-world.de/popups/popup_single_mediaplayer/0,,14815728_type_audio_struct_12103_contentId_6427031,00.html