አሜሪካኖች ባል ለሚስቱ ምን ያድርግ ይላሉ?
ከሰላዩ ብእር የቀጠለ
ክፍል አራት
ለባለቤቴ እጅግ ጥሩ ባል መሆን እንዳለብኝ ገና ድሮ በወጣትነት ዘመኔ ሳላገባ በፊት አስብ ነበር ፡፡ከዚሁ ጋር በተገናኘ ሀሳብ ብዙ መጻሕፍትን እንብቤአለሁ፡፡ ካነበብኩዋቸው መጻሕፍት ብዙ ዕውቀትና ምክርንም አግንቻለሁ፡፡ ለዚህ ነው ባለቤቴን በተቻለኝ ሁሉ ለማስደሰትና ለመንከባከብ ጥረት ያደረኩት ፡፡ ከባለቤቴ ጋር የነበረንን የሆቴል ቤት ቆይታ ትርኢት ከማጠቃለሌ በፊት ምናልባት አንባቢያን ትምህርት ታገኙበት ይሆናል በማለት አንድ መጽሔት ሳነብ ካገኘሁት ላካፍላችሁ ብዬ ይህንን የእንጊሊዘኛ ጽሑፍ ጋብዤአለሁና አንብቡት ፡፡የተዘረዘረውን ሁሉ ለመፈጸም ቢከብድም ጽሑፉ በትዳር ሕይወት ውስጥ ከሚስት ጋር ሰላማዊ ኑሮን ለመምራት ባል ማድረግ ያለበትንና ሚስት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ የሚዘረዝር ነውና አንብባችሁ የራሳችሁን ግንዛቤ ውሰዱ ፡፡